የፀሐይ ባንክ ባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

ለተከበራችሁ የፀሐይ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች

 

የፀሐይ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በንግድ ህግ አንቀፅ 366፣367፣370 እና 372 መሠረት ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔው እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 

የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት                       የባንክ ስራ ላይ የተሰማራ የአክሲዮን ማህበር

• የባንኩ የተፈረመ ካፒታል                     2,834,466,000

• የባንኩ የተከፈለ ካፒታል                      1,164,871,150

• የባንኩ የምዝገባ ቁጥር                         MT/AA/3/0052690/2014

• የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ            አዲስ አበባ፣ክ/ከ-ቂርቆስ ወረዳ 04 የቤት ቁ. አዲስ

 

የ2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1. የጉባዔ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፤

2. እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ ፤

3. እ.ኤ.አ. የ2022/23 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፓርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤

4. እ.ኤ.አ. የ2022/23 የውጭ ኦዲተሮችን ሪፓርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤

5. እ.ኤ.አ የ2023/24 የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል መወሰን ፤

6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላ አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት ማዳመጥና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን፤

7. የጉባዔውን ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ፤

 

ማሳሰቢያ፤

  • በጉባዔው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለአክሲዮን ከታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ግሎባል ሆቴል ፊትለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ምድር ወለል ላይ በሚገኝው የአክሲዮን አስተዳደር ዋና ክፍል ቀርበው የውክልና ቅጽ መሙላት ይችላሉ፡፡

 

  • እንዲሁም በውል እና ማስረጃ የተረጋገጠ በጉባዔ ላይ ለመካፈል እና ድምፅ ለመስጠት ግልፅ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በዕለቱ የውክልናውን ዋና እና ኮፒ እንዲሁም የባለአክሲዮኑን መታወቂያ ኮፒ ይዞ በመቅረብ በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ይችላል፡፡

 

  • በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውክልና በጉባዔው ላይ የሚገኙ ተወካዮች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ዋና እና ኮፒ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ፀሐይ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

 

ፀሐይ ባንክ ለሁሉ!