እንኳን አደረሰን!

ፀሐይ ባንክ በይፋ ሥራ ለጀመረበት ፪ኛ ዓመት እንኳን አደረሰን እያልኩ፤ ለባንካችን ስኬት የጀርባ አጥንት ለሆናችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን፣ ባለአክሲዮኖቻችን፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞቻችን ያለኝን አክብሮት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

 

ባንካችን ላስመዘገበው ውጤት የሁላችሁም አስተዋጽኦ የላቀ በመሆኑ፤ ከዚህ በበለጠ ለማሳካት ከጎናችን እንደምትቆሙ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡

 

የጀመርነውን እድገት አጠናክረን እንደምንቀጥል ስገልጽ በታላቅ ኩራት ነው፡፡ መልካም የስኬት ዓመት ይሁንልን፡፡

 

ያሬድ መስፍን
ዋና ሥራ አስፈጻሚ

 

ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!