ፀሐይ ባንክ በደብረብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

ፀሐይ ባንክ በደብረብርሃን ከተማ በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 72 ካርቶን የተመጣጠነ የአልሚ ምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡

ባንኩ ድጋፉን ያደረገው ቪታባይት ኒዩትሪሽን ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ሲሆን፣ ድጋፉ በተለይ አልሚ ምግብ የሚሹ ሕፃናትን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመላ ሀገሪቱ ከ82 በላይ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ፀሐይ ባንክ፤ በመሰል ማኅበራዊ አገልግሎቶችም እየተሳተፈ ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡

 

ፀሐይ ባንክ

ለሁሉ!