[GTranslate]

Advert

የባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ !

ለተከበራችሁ የፀሐይ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች

የፀሐይ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በንግድ ህግ አንቀፅ 366፣ 367፣ 370 እና 372 መሠረት ታኅሣስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባኤው እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 

  • የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት………… የባንክ ስራ ላይ የተሰማራ የአክሲዮን ማኅበር
  • የባንኩ የተፈረመ ካፒታል ……………. ብር 2,837,466,000.00
  • የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ……………. ብር 734,744,000.00
  • የባንኩ የምዝገባ ቁጥር ………………MT/AA/3/0052690/2014
  • የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ፣ክ/ከ/ቂርቆስ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር አዲስ

 

የ1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም
  2. ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ
  3. የጉባዔ አጀንዳዎችን ማፅደቅ
  4. እስከ ታኅሣስ 5 ቀን 2015 ዓ.ም . ድረስ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ
  5. የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
  6. የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ
  7. እ.ኤ.አ. ከ2022/23 እስከ 2024/25 በጀት ዓመት ድረስ የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና ክፍያቸውን መወሰን
  8. እ.ኤ.አ. የ2022/23 የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል መወሰን
  9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ዕጩዎች ማቅረቢያና ምርጫ ማስፈፀሚያ መመሪያ ማፅደቅ እና የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ የስራ ዋጋና አበል መወሰን
  10. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ማከናወን እና
  11. የጉባዔውን ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ

 

የ1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም
  2. ምልዓተ ጉባዔው መሟላቱን ማረጋገጥ
  3. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማፅደቅ
  4. የባንኩን የተፈረመ ካፒታል አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን
  5. የባንኩን ካፒታል ማሳደግ
  6. የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል እና
  7. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ

 

ማሳሰቢያ ፡-

  • በጉባዔው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለአክሲዮን እስከ ታኅሣስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ግሎባል ሆቴል ፊትለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 8ተኛ ፎቅ ሕግ አገልግሎት መምሪያ ቀርበው የውክልና ቅጽ መሙላት ይችላሉ፡፡
  • እንዲሁም በውል እና ማስረጃ የተረጋገጠ በጉባዔ ላይ ለመካፈል እና ድምፅ ለመስጠት ግልፅ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በዕለቱ የውክልናውን ዋና እና ኮፒ ይዞ በመቅረብ በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ይችላል፡፡
  • በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውክልና በጉባዔው ላይ የሚገኙ ተወካዮች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ዋና እና ኮፒ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
    ፀሐይ ባንክ አ.ማ.

 

የዳይሬክተሮች ቦርድ