[GTranslate]

ፀሐይ ባንክ አ.ማ.
አክስዮኖችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

 ፀሐይ ባንክ አ.ማ.  አክሲዮን ለመግዛት ፈርመው ክፍያቸውን በተቀመጠው የክፍያ መርሃ ግብር ያልተከፈሉ አክሲዮኖችን በንግድ ሕጉ መሰረት  በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. የአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 1000 ( አንድ ሺ ) ሲሆን የአንድ አክስዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1050.00 (አንድ ሺ ሀምሳ ብር ) ነው፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው መግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክስዮን ብዛት 100 (አንድ መቶ) ነው፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚገዙት እያንዳንዱ አክሲዮን የሚከፍሉት ተጨማሪ የክፍያ መጠን በግልፅ ማመልከት አለባቸው፡፡
  4. በኢትዮጵያዊን ወይም በትውልደ ኢትዮጵያዊያን የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ወይም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ወይም በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወይም በኢትዮጵያውያን እና በትውልደ ኢትዮጵያዊያን  የተያዙ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ እና አክሲዮኖችን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉት አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከየትኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች ወይም ደብረ ዘይት መንገድ መዓዛ ደሳለኝ ህንፃ ላይ ከሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት  የአክሲዮን አስተዳደር ዋና ክፍል በመገኘት ከግንቦት 7  ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሠነዶችን በመውሰድ፣ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ  ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ድረስ በየትኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች ወይም በባንኩ ዋና መ/ቤት  በሚገኘው አክሲዮን አስተዳደር ዋና  ክፍል ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በደብረዘይት መንገድ በሚገኘው መዓዛ ህንፃ 5ኛ ፎቅ በባንኩ በፋይናንስ እና ሂሳብ መምሪያ ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ አክሲዮኖቹን የሚጫረቱበትን ዋጋ 5 በመቶ ወይም ከፍተኛ አክሲዮን በመግዛት ለሚጫረቱ 500,000( አምስት መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚገዙበትን ዋጋ ከሚገልፁበት ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአክሲዮን ግዢ ክፍያው ይውላል፡፡
  8. ተጫራቾች አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  9. ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፖስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ እንዲሁም ድርጅቶች ከሆኑ አክሲዮኖቹ በሙሉ ኢትዮጵያዊ በሆኑ ዜጐች የተያዙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የመመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ተቀባይነት ያለው ሰነድ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወይም በትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጪ ሀገር ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች የተቋቋመ ድርጅት አክሲዮን ለመግዛት ክፍያ የሚፈጽሙት በተፈቀደ የውጭ ምንዛሪ ብቻ ይሆናል፡፡
  11. ኢትዮጵያዊ ዜግነት ወይም የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  12. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ15 ( አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  14. ማንኛውም በጨረታ አፈፃፀም ሊፈጠር የሚችል አለመግባባት ቢከሰት አግባብነት ያላቸው ሕጐችና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
  15. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

                                                                        ፀሐይ ባንክ አ.ማ

                     

                                           Addis Ababa, Kirkos Sub-city, Woreda 04, Meaza Desalegn Building 

Phone: +251 114 705273

Fax: +251 114 706152

P.O.Box: 2506

Email: info@tsehaybank.com.et

                                                                  Tsehay Bank

                                                           Addis Ababa, Ethiopia