- Contact Us
- Branch/ATM
- Daily Exchange Rate
- Loan Calculator
- SWIFT Code: TSCPETAA
- Vacancy
1. Definition
a. Mobile Banking: – shall mean a service that allows customers use their mobile device to access banking services.
b. The Bank: – shall mean Tsehay Bank S.C.
2. Governing Law
a. This terms and conditions shall be governed and constructed in accordance with the laws of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, applicable Directives of the National Bank of Ethiopia and pertinent policies and procedures issued by Tsehay Bank S.C.
3. General Provisions
a. The customer shall be bound by the terms and conditions of this agreement upon registering or subscribing to use mobile banking services through his/her mobile phone.
b. The Bank reserves the right to limit and vary the amount and frequency of payments that a customer may make by using the mobile banking service without prior notice to the customer.
c. The customer acknowledges that the mobile banking service is dependent on the infrastructure, connectivity and services provided by the telecom service provider.
d. The customer accepts that timeliness, accuracy and readability of SMS and information shall depend on factors affecting the telecom service provider.
e. The customer shall ensure that the Bank’s charges are always duly paid to the Bank and the Bank shall be entitled to debit the customer’s bank account or recover it’s charges from the customer in any manner it deems fit.
f. The customer can unsubscribe from the service at any time.
4. Restriction on use
a. The customer acknowledges not using mobile banking service for any illegal, fraudulent and unauthorized purpose and will only be used in compliance with all applicable laws, rules and regulations of the country and the Bank.
b. If the Mobile Banking User becomes inactive for a period of six (6) consecutive months, the bank reserves the right to remove it from the system. To reactive it, the customer shall need to enroll again.
c. To use Tsehay Bank’s Mobile Banking service, the mobile number should be the one which is registered in the name of the customer.
5. Confidentiality and Disclosure
a. The parties hereby undertake to maintain the confidentiality of each other’s information. However, to the extent permitted by law, the bank shall be entitled to transfer any information relating to the customer to its representatives, affiliates or auditors wherever situated for confidential use and in connection with the mobile banking service.
b. The Bank shall be entitled at any time to disclose any information concerning the customer within the knowledge and possession of the Bank to courts and legally authorized government offices and agencies.
c. The customer undertakes to maintain the strict confidentiality of his/her mobile banking service PIN/Password.
6. Indemnity
a. The customer agree to indemnify, defend and hold the bank harmless from and against any claims, losses, liability and expenses arising from customer’s use of mobile banking service.
7. Limitation of Liability
a. Without prejudice to any other provisions of this terms and conditions, the Bank shall not be liable to the customer for any loss or damage whatsoever or howsoever be used arising directly or indirectly in connection with customer’s use of mobile banking service.
8. Records of the Bank
a. The customer agrees that the Bank’s recording of transactions and operations made or processed through mobile banking services by the customer or any person acting on behalf of the customer with or without the customer’s consent shall be binding and conclusive on the customer.
b. In case the customer considers that there has been an error or irregularity in the recording system of the Bank, he/she will be allowed to inform the Bank. However, if the customer has not informed the Bank in writing of any error contained in any account statement within Five (5) days of the date on which the customer’s account was credited or debited, the customer shall be deemed to have accepted the evidence.
c. The customer acknowledges and agrees that printed and signed PDF format documents sent by e-mail by the Bank shall be deemed to be written documents and shall have the same evidential value as original documents.
9. Warranty
a. The Bank makes no implied warranty with respect to customer’s mobile banking service usage.
10. Termination
a. The Bank reserves the right to terminate any or all of the mobile banking services at any time without prior notice. The Bank also reserves the right to alter or modify all or part of these terms and conditions at any time without prior notice.
b. The Bank may suspend or terminate the service to customers if it believes that the customer is in breach of the terms and conditions.
11. Effective Date
a. The customer shall be bound by these terms and conditions upon signing and subscribing to the Mobile Banking Service.
1. ትርጓሜ
1.1. ሞባይል ባንኪንግ:- ማለት ደንበኞች የሞባይል ስልካቸውን ተጠቅመው የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አገልግሎት ማለት ነው፡፡
1.2. ባንክ፡- ማለት ፀሐይ ባንክ አ.ማ ማለት ነው፡፡
2. ገዥ
ህጎች
2.1. ይህ ደንብ እና ሁኔታ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ህግ መሰረት፣በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ መመርያዎች እና በፀሐይ ባንክ አ.ማ በሚወጡ አግባብነት ያላቸው ፖሊሲዎች የአሰራር መመሪያዎች መሰረት የሚመራ የሚተገበር ይሆናል፡፡
3. ጠቅላላ ድንጋጌ
3.1. ደንበኛው በተንቀሳቃሽ ስልኩ አማካኝነት አገልግሎቱን ለመጠቀም ሲመዘገብ በዚህ ስምምነት መሰረት የሚመራ ይሆናል፡፡
3.2. ባንኩ ለደንበኛው አስቀድሞ ማሳወቅ ሳይጠበቅበት የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን በመጠቀም ደንበኛው ሊከፍል የሚችለውን የክፍያ መጠንና ብዛት የመገደብ እና የመቀያየር መብት አለው፡፡
3.3. ባንኩ የሚያቀርበው የሞባይል ባንክ አገልግሎት የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢው በሚያቀርበው የመሰረተ ልማት፣ መገናኛና አገልግሎት ላይ ጥገኛ መሆኑን ደንበኛው አምኖ ይቀበላል፡፡
3.4. ደንበኛው የሚያገኘው የአጭር መልዕክት (SMS) እና መረጃ ወቅታዊነት፣ ትክክለኛነት እና ተነባቢነት በቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢው ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ነገሮች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ይቀበላል፡፡
3.5. ደንበኛው የባንኩ ክፍያ ሁሌም ለባንኩ በአግባቡ እንዲከፈል እና ባንኩ ተገቢ መስሎ በታየው በማንኛውም መንገድ ከደንበኛው ላይ ያለውን ክፍያ የማስመለስ መብት እንዲኖረው ለማድረግ ተስማምቷል፡፡
3.6. ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ አገልግሎቱን ማቋረጥ ይችላል፡፡
4. የአጠቃቀም ገደብ
4.1. ደንበኛው የባንኩን ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን ለማንኛውም ህገ ወጥ፣ የተጭበረበረ እና ያልተፈቀደ ዓላማ ላለመጠቀም እና በሀገሪቱ እንዲሁም በባንኩ ውስጥ ተግባራዊ የሆኑ ህጎች እና ደንቦችን በሙሉ በማክበር ለመጠቀም ተስማምቷል፡፡
4.2. የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚው ለተከታታይ ስድስት (6) ወራት አገልግሎቱን ካልተጠቀመ ባንኩ ተጠቃሚውን ከሲስተም የማስወገድ መብት አለው። ደንበኛው አገልግሎቱን በድጋሜ መጠቀም ከፈለገ እንደገና መመዝገብ ያስፈልገዋል፡፡
4.3. የባንኩን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ለመጠቀም የሚቀርበው የሞባይል ቁጥር በደንበኛው ስም የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡
5. ምስጢራዊነት
5.1. ተስማሚ ወገኖች አንዳቸው የሌላውን መረጃ ምስጢራዊነት ይጠብቃሉ፡፡ ነገር ግን ባንኩ በሕጉ በተፈቀደለት መጠን ከደንበኛው ጋር የተያያዘ ማንኛውንም መረጃ ከደንበኛው እና/ወይም ከደንበኛው የሞባይል ባንኪንግ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ደንበኛው የሚሰጠውን ማንኛውንም ሌላ መረጃ ለሚስጥራዊ አገልግሎት በሚውልበት ቦታ ሁሉ ለወኪሎቹ ወይም ለኦዲተሮቹ የማስተላለፍ መብት አለው፡፡
5.2. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ በባንኩ ዕውቀትና ይዞታ ውስጥ ያለውን ደንበኛ በተመለከተ ማንኛውንም መረጃ ለፍርድ ቤቶችና በሕግ ለተፈቀደላቸው የመንግስት ቢሮዎችና ድርጅቶች የማሳወቅ መብት አለው፡፡
5.3. ደንበኛው ለሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የሚጠቀምበትን ሚስጥር ቁጥር ወይም የይለፍ ቃል ሚስጥራዊነት የመጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡
6. ከለላ
6.1. ደንበኛው ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አጠቃቀሙ ጋር በተያያዘ ባንኩን ከማንኛውም ክስ፣ ኪሳራ፣ ሃላፊነት እና ወጪ ለመጠበቅ እና ለመከላከል ተስማምቷል፡፡
7. የኃላፊነት ውስንነት
7.1. ባንኩ ከደንበኛው የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሚነሳ ማንኛውም ኪሳራ ወይም ጉዳት ለደንበኛው ተጠያቂ አይሆንም፡፡
8. የባንኩ መዛግብት
8.1. በባንኩ የተመዘገቡ እና በደንበኛው ወይም በደንበኛው ወኪል አማካኝነት በሞባይል ባንኪንግ የሚሰሩና የሚከናወኑ የንግድ ልውውጦች እና ስራዎች በደንበኛው እንደተፈፀሙ እንደሚቆጠር ደንበኛው ተስማምቷል፡፡
8.2. ደንበኛው በባንኩ የሂሳብ መግለጫ ላይ ስህተት ወይም አለመጣጣም መኖሩን ቢያስብ ለባንኩ እንዲያሳውቅ ይፈቀድለታል። ይሁን እንጂ ደንበኛው የደንበኛው አካውንት ገቢ ወይም ተቀናሽ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ቀናት ውስጥ በማንኛውም የሒሳብ መግለጫ ውስጥ የተካተተውን ማንኛውንም ስህተት ለባንኩ በጽሑፍ ካላሳወቀ ደንበኛው ማስረጃውን እንደተቀበለ ይቆጠራል፡፡
8.3. ደንበኛው ከባንኩ በኢ-ሜይል የሚላኩለትን መልዕክቶች ወይም የተፈረሙ የፒዲኤፍ ኮፒዎች በጽሑፍ እንደሰፈረ ሰነድ ተደርጎ እንዲቆጠር እና ከመጀመሪያ ሰነዶች ጋር ተመሳሳይ የሆነ የማስረጃ ዋጋ እንዳለው ይስማማል፡፡
9. ዋስትና
9.1. ባንኩ የደንበኞችን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አጠቃቀም በተመለከተ ምንም ዓይነት ዋስትና አያቀርብም፡፡
10. የአገልግሎት መቋረጥ
10.1. ባንኩ ማንኛውንም ወይም ሁሉንም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ በማንኛውም ጊዜ የማቋረጥ መብት አለው። በተጨማሪም ባንኩ የዚህን ደንብና ሁኔታ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ በሙሉ ወይም በከፊል የመለወጥ ወይም የማስተካከል መብት አለው።
10.2.
ባንኩ ደንበኛው የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ደንብና ሁኔታዎችን ጥሷል ብሎ ካመነ አገልግሎቱን ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሊያቋርጥ ይችላል::
11. ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ የሚሆኑበት ቀን
11.1. ደንበኛው ለሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚነት ፈርሞ ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ደንብና ሁኔታ ተገዠ ለመሆን ተስማምቷል
Welcome to Teshay Bank!
Dear Customer, What can I help you?
Tsehay Bank ©️ 2024 All Rights Reserved.