- Contact Us
- Branch/ATM
- Daily Exchange Rate
- Loan Calculator
- SWIFT Code: TSCPETAA
- Vacancy
በጉባኤው ላይ የባንኩ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት የሒሳብ ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች የቀረበ ሲሆን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫም ተከናውኗል፡፡
ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ በዋና ዋና የአፈጻጸም መለኪያዎች እና በላቀ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ስኬታማ እንደነበር የቀረበው ሪፖርት ያሳያል። ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ አበረታች ትርፍ ያስመዘገበ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ደንበኞች፣ የፈጅር ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች እንዲሁም የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር መጨመሩ ተመላክቷል፡፡
በሒሳብ ዓመቱ የባንኩ የተጣራ ብድርና ከወለድ ነጻ የፋይናንሲንግ አቅርቦት እድገት ማሳየቱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ገቢ እድገት የታየበት ሲሆን በአጠቃላይ ወጪ አስተዳደር የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡም ተመላክቷል።
ተለዋዋጭ በሆነው የሀገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውጤታማ ለመሆን ከአዳዲስ መመሪያዎች ጋር አሠራሩን በማጣጣም በርካታ ጥረቶችን እያደረገ እንደሚገኝ የባንኩ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አየነው ገልጸዋል።
በዚህም ባንኩ አዲስ የሦስት ዓመት ኮርፖሬት ስትራቴጂ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ ሲሆን ስድስት የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ዘላቂ የቢዝነስ እድገት፣ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት፣ ዲጂታላይዜሽን፣ የአሠራር ቅልጥፍና፣ ሪስክ አስተዳደር እና የሰው ሃብት ልማትና ተቋማዊ ባህል ባንኩ በትኩረት የሚሠራባቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተገልጿል።
ባንኩ የተከፈሉ አክሲዮኖችን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለማስመዝገብ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!
Welcome to Teshay Bank!
Dear Customer, What can I help you?

Tsehay Bank ©️ 2026 All Rights Reserved.