- Contact Us
- Branch/ATM
- Daily Exchange Rate
- Loan Calculator
- SWIFT Code: TSCPETAA
- Vacancy
ነፃ እና ለሁሉም ክፍት የሆነ ገመድ አልባ ኢንተርኔት (Public/Free WiFi) በብዙ ቦታዎች እየተስፋፋ የመጣ ሲሆን በርካታ ተገልጋዮችንም አፍርቷል። በአንፃሩ አብዛኞቹ ተጠቃሚዎች በዚሁ አውታረ መረብ ውስጥ በእነርሱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሊከናውን እንደሚችል በቂ ግንዛቤ እና መረጃ የላቸውም። በመሆኑም መሰል የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለሁሉም አይነት ፍላጎቶቻቸው ሲያውሉት ይታያል።
ለሁሉም ሰው ክፍት የሆነ፣ ነፃ እና ገመድ አልባ ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚደረግ የዲጂታል ባንክ አጠቃቀም ለገንዘብ እና ለመረጃ ስርቆት ሊዳርግ የሚችልበት ሠፊ ዕድል አለው። በመሆኑም ደንበኞች ይህንን አይነት የኢንተርኔት ግንኙነት ሲጠቀሙ የዲጂታል የባንክ መተግበሪያዎችን እና ድረ-ገፆችን ከመክፈትም ሆነ ከመጠቀም ሊቆጠቡ ይገባል።
“ለዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች እና ግብይቶች ነፃ ዋይ ፋይን /Free Wi-Fi በፍጹም አይጠቀሙ!”
ከፀሐይ ባንክ የዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ለሚያጋጥሞ ማንኛውም ዓይነት የደህንነት ስጋት ወይም ችግር ጥቆማዎን ለባንካችን በስልክ ቁጥር +251-114-706158 ወይም በኢሜል አድራሻችን info@tsehaybank.com.et ይላኩልን፡፡ን፡፡
ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!
ብዙዎቻችን የኢንተርኔት የባንክ የይለፍ ቃላችንን (Password) ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በተደጋጋሚ ሰምተናል፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የብዙዎቻችን ጠባይ ይህን እውቀት አይያንጸባርቅም፡፡ የዕለት ተዕለት ተግባራት እና ጥናታዊ ጽሁፎች ወይም ዳሠሳዎች እንደሚያሳዩን አብዛኛው የሞባይል፣ የኢንተርኔት እና የATM ካርድ ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃላቸውን ለጓደኛ ወይም ለቤተሰብ አባል ያጋራሉ/ይነግራሉ/፡፡ ወይንም ተመሳሳይ የይለፍ ቃል ለተለያዩ የባንክ አገልግሎቶች ይጠቀማሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ተገልጋዮች ደግሞ የሚጠቀሟቸው የይለፍ ቃላት ጠንካራ ውህደት/ጥምረት የላቸውም፡፡
እንደ እነዚህ ዓይነት የማይመከሩ የይለፍ ቃል ልማዶችን የሚተገብሯቸው ከሆነ ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም እንዴት እንደሚያሻሽሏቸው እናግዝዎ…
ምክር 1፡ የይለፍ ቃልዎ ከስድስት ፊደላት በላይ እንዲረዝም ያድርጉ፡፡
ምክር 2፡ ጠንካራ ውህድ/ጥምረት ይጠቀሙ – ቁጥሮች እና ምልክቶች የተካተቱበት ቢሆን ይመረጣል፡፡
ምክር 3፡ የልጆች፣ የባለቤት፣ በቅርብ ያሉ የቤተሰብ አባላትን ስሞች፣ የልደት ቀናት ወይም ሌሎች የግል መረጃዎችን እንዲሁም የተለመዱ ቃላትን ወይም ሌሎች ሊገምቱት የሚችሉትን የይለፍ ቃላት አይጠቀሙ፡፡
ምክር 4፡ ለተለያዩ የባንክ አገልግሎቶች የተለያየ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ፡፡
ምክር 5፡ ለወዳጅ እና ቤተሰብዎ ከማጋራት (share ከማረግ) ይቆጠቡ፡፡
ምክር 6፡ የይለፍ ቃልዎ ጠንካራ ውህደት የሚያስታውሱትን ያህል መሆን ይገባዋል፡፡
ከፀሐይ ባንክ የዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ለሚያጋጥሞ ማንኛውም ዓይነት የደህንነት ስጋት ወይም ችግር ጥቆማዎን ለባንካችን በስልክ ቁጥር +251-114-706158/+251-114-706854 ወይም በኢሜል አድራሻችን info@tsehaybank.com.et ይላኩልን፡፡
ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት የሚታዩ የደንበኞች ሂሳብ ላይ ያነጣጠሩ የማጭበርበር ወንጀሎች ተበራክተዋል። ለዚህ ጥቃት ዒላማ ለመሆን የባንክ ደንበኝነት ብቻ በቂ ነው።
ውድ የፀሐይ ባንክ ደንበኛችን ከዚህ እና መሠል ጥቃቶች እራስዎን ለመጠበቅ እባክዎትን የሚከተሉትን መርሆች ይከተሉ፦
• ከባንክ በማስመሰል ስልክ በመደወል የተለያዩ አገልግሎቶች ጀምረናል በሚል እና መሰል የማጭበርበሪያ ስልቶች በመጠቀም ከሂሳብዎት ላይ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ ሲጠየቁ ባንኩ ይህ ዓይነት አሰራር ስለሌለው እንደማያስተላልፉ ይግለጹ፡፡ ጥቆማዎን ለባንካችን በስልክ ቁጥር +251 114 -705273 ወይም በኢሜል አድራሻችን info@tsehaybank.com.et ይላኩልን፡፡
• ከባንክ የተደወለ በማስመሰል ወይም የግል ሚስጥራዊ መረጃዎችን እና የይለፍ ቃል በስልክ ሲጠየቁ በፍጹም አይናገሩ!
• ለባንካችንም ሰራተኞችም ይሁን ለሌላ ግልሰብ የግል ሚስጥራዊ የይለፍ ቃላት ወይም ቁጥሮች (password or PIN ) በፍጹም አይግለጹ!
ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!
Welcome to Teshay Bank!
Dear Customer, What can I help you?
Tsehay Bank ©️ 2024 All Rights Reserved.