- Contact Us
- Branch/ATM
- Daily Exchange Rate
- Loan Calculator
- SWIFT Code: TSCPETAA
- Vacancy
የፀሐይ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሒዷል፡፡
በጉባኤው ላይ የባንኩን ዓመታዊ ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አየነው እንደገለጹት፤ ፀሐይ ባንክ የፋይናንስ ኢንዱስትሪውን በተቀላቀለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘመኑን የዋጀ፣ ቀልጣፋ፣ እና ደኅንነቱ አስተማማኝ የሆነ የባንክ አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ በከፈታቸው 91 ቅርንጫፎች እየሰጠ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ዘመናዊ የሆኑ የዲጂታል እና የካርድ ባንኪንግ አገልግሎቶችን ተግባራዊ በማድረግ ደንበኞች በጊዜ እና በቦታ ሳይገደቡ የባንክ አገልግሎት እየተጠቀሙ መሆኑን ገልጸዋል።
ባንኩ 510,000 የሚጠጉ ደንበኞች በማፍራት፤ ብር 4.3 ቢሊዮን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ የቻለ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ89 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አቶ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡
በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ለሚገኙ የባንኩ ደንበኞች አጠቃላይ የተሰጠው ብድር ብር 1.7 ቢሊዮን መሆኑን የገለጹት የቦርድ ሰብሳቢው፤ የባንኩ የተጣራ ብድር ብር 2.51 ቢሊዮን መድረሱን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ በድምሩ ብር 2.95 ቢሊዮን ዋጋ ያላቸው ዋስትናዎች ለደንበኞቹ አቅርቧል፡፡
በሒሳብ ዓመቱ ከበርካታ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ የኮረስፖንደንት ባንኮች እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ጋር በመስራት፤ 40.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የቻለ ሲሆን፤ በተለያዩ ዘርፎች ለሚገኙ ደንበኞቹ 35.4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ አቅርቧል፡፡
የቦርድ ሰብሳቢው እንደገለጹት፤ የፋይናንስ አካታችነትን ማስፋት፣ ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ የዲጂታል የባንክ አገልግሎት አማራጮችን ማቅረብ እንዲሁም የካፒታል አቅምን ማጠናከር፤ ባንኩ ወደፊት በትኩረት የሚሠራባቸው ጉዳዮች ናቸው።
ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!
Welcome to Teshay Bank!
Dear Customer, What can I help you?

Tsehay Bank ©️ 2026 All Rights Reserved.