የፀሐይ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ

ለተከበራችሁ የፀሐይ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች

ፀሐይ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 366(1)፣ 367(1)፣370 እና 372 እንዲሁም በባንኩ የተሻሻለው የመመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 18 መሠረት ታኅሣሥ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል ይካሄዳል::

በመሆኑም የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በዕለቱ በጠቅላላ ጉባዔው እንድትገኙልን የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

1. ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች

1.1  የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ               አዲስ አበባ፣ክ/ከ-ቂርቆስ ወረዳ 04 የቤት ቁ. አዲስ 
1.2  የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት                      የባንክ ስራ ላይ የተሰማራ የአክሲዮን ማህበር
1.3  የባንኩ የምዝገባ ቁጥር                        MT/AA/3/0052690/201
1.4  የባንኩ የተፈረመ ካፒታል                      2,834,466,000.00
1.5  የባንኩ የተከፈለ ካፒታል                      1,284,442,250.00

2. የ4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

2.1. እስከ ታኅሣሥ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅና ማጽደቅ፤

2.2. እ.ኤ.አ. የ2024/25 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፓርት ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤

2.3. እ.ኤ.አ. የ2024/25 የውጭ ኦዲተሮችን ሪፓርት ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤

2.4. እ.ኤ.አ የ2025/26 የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል መወሰን፤

2.5. እ.ኤ.አ. ከ2025/26 እስከ 2027/28 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተር መሾምና የአገልግሎት ክፍያውን መወሰን፤

2.6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና ምርጫ ማስፈፀሚያ የአሠራር ደንብ ረቂቅ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

ማሳሰቢያ፤

3.1. በጉባዔው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለአክሲዮን ከታኅሣሥ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በቅሎ ቤት አካባቢ የቀድሞው ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት  በሚገኘው የአክሲዮን አስተዳደር ዋና ክፍል ቀርቦ የውክልና ቅጽ መሙላት ይችላል፡፡

3.2. እንዲሁም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የተረጋገጠ በጉባዔ ላይ ለመካፈል እና ድምፅ ለመስጠት ግልፅ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በዕለቱ የውክልናውን ዋና እና ኮፒ እና የባለአክሲዮኑን መታወቂያ ኮፒ ይዞ በመቅረብ በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ይችላል፡፡

3.3. በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ፣  ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውክልና በጉባዔው ላይ የሚገኙ ተወካዮች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ዋና እና ኮፒ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

3.4. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅ ላይ በተደነገገው መሠረት ተገቢውን መረጃ ለማሟላት እንዲረዳ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) እና የታክስ መለያ ቁጥር መታወቂያ (TIN) ዋናውን እና ኮፒውን በመያዝ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

3.5. በአጀንዳ ንዑስ ቁጥር 2.6 የተመለከተውን ሰነድ የባንኩ ድረ ገጽ ላይ  https://tsehaybank.com.et/wp-content/uploads/2025/12/Guidelines-for-Nominating-and-Electing-Candidates-to-the-Board-of-Directors.pdf በዚህ ማስፈንጠሪያ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ፀሐይ ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ